ዘኁልቍ 26:44-57 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

44. የአሴር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በዩምና በኩል፣ የዩምናውያን ጐሣ፣በየሱዋ በኩል፣ የየሱዋውያን ጐሣ፣በበሪዓ በኩል፣ የበሪዓውያን ጐሣ፤

45. እንዲሁም በበሪዓ ዘሮች በኩል፣በሔቤር በኩል፣ የሔቤራውያን ጐሣ፣በመልኪኤል በኩል፣ የመልኪኤላውያን ጐሣ።

46. አሴር ሤራሕ የምትባል ልጅ ነበረችው።

47. እነዚህ የአሴር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

48. የንፍታሌም ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በያሕጽኤል በኩል፣ የያሕጽኤላውያን ጐሣ፣በጉኒ በኩል፣ የጉናውያን ጐሣ፣

49. በሺሌም በኩል፣ የሺሌማውያን ጐሣ፤

50. እነዚህ የንፍታሌም ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት አርባ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

51. ባጠቃላይ የእስራኤል ወንዶች ቍጥር ስድስት መቶ አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበር።

52. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

53. “ምድሪቱ በስማቸው ቍጥር ልክ ተደልድላ በርስትነት ለእነርሱ ትሰጥ።

54. በርከት ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ሰፋ ያለውን ርስት፣ አነስ ያለ ቊጥር ላለው ጐሣ ደግሞ አነስ ያለውን ስጥ፤ ርስቱንም እያንዳንዱ በዝርዝሩ ላይ በተመለከተው ቊጥር መሠረት ይረከባል።

55. የመሬት ድል ድሉም በዕጣ ይሁን፤ እያንዳንዱ የሚወርሰውም በየነገድ አባቶቹ ስም ይሆናል።

56. እያንዳንዱም ርስት በትል ልቆቹና በትንንሾቹ ነገዶች መካከል በዕጣ ይደለደላል።

57. በየጐሣቸው የተቈጠሩት ሌዋውያን እነዚህ ነበሩ፤በጌድሶን በኩል፣ የጌድሶናውያን ጐሣ፣በቀዓት በኩል፣ የቀዓታውያን ጐሣ፣በሜራሪ በኩል፣ የሜራራውያን ጐሣ፤

ዘኁልቍ 26