4. “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
5. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤
6. በአስሮን በኩል፣ የአስሮናውያን ጐሣ፤በከርሚ በኩል፣ የከርማውያን ጐሣ፤
7. እነዚህ የሮቤል ጐሣዎች ሲሆኑ፤ ከእነዚህም የተቈጠሩት አርባ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሠላሳ ነበሩ።
8. የፈሉስ ልጅ ኤልያብ ሲሆን፣
9. የኤልያብ ልጆች ደግሞ፣ ነሙኤል ዳታንና አቤሮን ነበሩ። እነዚሁ ዳታንና አቤሮን በሙሴና በአሮን ላይ ያመፁ የማኅበሩ ሹማምት ሲሆኑ፣ ቆሬና ተከታዮቹ በእግዚአብሔር (ያህዌ) ላይ ባመፁ ጊዜ እነርሱም በነገሩ ነበሩበት።
10. ሁለት መቶ አምሳዎቹን ሰዎች እሳት በበላቻቸው ጊዜ የቆሬ ተከታዮች ሲሞቱ እነዚህን ደግሞ ምድር ተከፍታ ከእርሱ ጋር ዋጠቻቸው፤ መቀጣጫም ሆኑ፤
11. የቆሬ የዘር ሐረግ ግን አልጠፋም።
12. የስምዖን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በነሙኤል በኩል፣ የነሙኤላውያን ጐሣ፤በያሚን በኩል፣ የያሚናውያን ጐሣ፤በያኪን በኩል፣ የያኪናውያን ጐሣ፤
13. በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤በሳኡል በኩል፣ የሳኡላውያን ጐሣ፤
14. እነዚህ የስምዖን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩትም ሃያ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።
15. የጋድ ዘሮች በየጐሣዎቻቸው እነዚህ ነበሩ፤በጽፎን በኩል፣ የጽፎናውያን ጐሣ፤በሐጊ በኩል፣ የሐጋውያን ጐሣ፤በሹኒ በኩል፣ የሹናውያን ጐሣ፤
16. በኤስና በኩል፣ የኤስናናውያን ጐሣ፤በዔሪ በኩል፣ የዔራውያን ጐሣ፤
17. በአሮዲ በኩል፣ የአሮዳውያን ጐሣ፤በአርኤሊ በኩል፣ የአርኤላውያን ጐሣ፤
18. እነዚህ የጋድ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከነዚህ የተቈጠሩት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።
19. ዔርና አውናን የይሁዳ ልጆች ነበሩ፤ ነገር ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል።