ዘኁልቍ 26:23-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣በፋዋ በኩል፣ የፋዋውያን ጐሣ፣

24. በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤

25. እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።

26. የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤

27. እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

28. የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤

29. የምናሴ ዘሮች፤በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤

30. የገለዓድ ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በኢዔዝር በኩል፣ የኢዓዝራውያን ጐሣ፣በኬሌግ በኩል፣ የኬሌጋውያን ጐሣ፣

31. በአሥሪኤል በኩል፣ የአሥሪኤላውያን ጐሣ፣በሴኬም በኩል፣ የሴኬማውያን ጐሣ፣

32. በሸሚዳ በኩል፣ የሸሚዳውያን ጐሣ፣በኦፌር በኩል፣ የኦፌራውያን ጐሣ፣

33. የኦፌር ልጅ ሰለጰዓድ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ ልጆቹ ሴቶች ብቻ ነበሩ፤ እነርሱም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካና ቲርጻ ይባላሉ።

ዘኁልቍ 26