20. የይሁዳ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሎም በኩል፣ የሴሎማውያን ጐሣ፤በፋሬስ በኩል፣ የፋሬሳውያን ጐሣ፤በዛራ በኩል፣ የዛራውያን ጐሣ፤
21. የፋሬስ ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በኤስሮም በኩል፣ የኤስሮማውያን ጐሣ፤በሐሙል በኩል፣ የሐሙላውያን ጐሣ፤
22. እነዚህ የይሁዳ ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሰባ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።
23. የይሳኮር ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በቶላ በኩል፣ የቶላውያን ጐሣ፣በፋዋ በኩል፣ የፋዋውያን ጐሣ፣
24. በያሱብ በኩል፣ የያሱባውያን ጐሣ፣በሺምሮን በኩል፣ የሺምሮናውያን ጐሣ፤
25. እነዚህ የይሳኮር ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ አራት ሺህ ሦስት መቶ ነበሩ።
26. የዛብሎን ዘሮች በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤በሴሬድ በኩል፣ የሴሬዳውያን ጐሣ፤በኤሎን በኩል፣ የኤሎናውያን ጐሣ፣በያሕልኤል በኩል፣ የያሕልኤላውያን ጐሣ፤
27. እነዚህ የዛብሎን ጐሣዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ የተቈጠሩት ሥልሳ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።
28. የዮሴፍ ዘሮች በምናሴና በኤፍሬም በኩል ያሉት በየጐሣቸው እነዚህ ነበሩ፤
29. የምናሴ ዘሮች፤በማኪር በኩል፣ የማኪራውያን ጐሣ፤ ማኪርም የገለዓድ አባት ነው፤በገለዓድ በኩል፣ የገለዓዳውያን ጐሣ፤