1. ከመቅሠፍቱ በኋላ እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና የካህኑን የአሮንን ልጅ አልዓዛርን እንዲህ አላቸው፤
2. “ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን፣ በእስራኤልም ጦር ሰራዊት ውስጥ ለማገልገል ብቃት ያላቸውን ሁሉ ከመላው የእስራኤል ማኅበረሰብ ከየቤተ ሰቡ ቊጠሩ።”
3. ስለዚህ ሙሴና ካህኑ አልዓዛር ከኢያሪኮ ማዶ በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው በሞዓብ ሜዳ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፤
4. “እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን ባዘዘው መሠረት ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያ በላይ የሆነውን ቍጠሩ።”ከግብፅ የወጡት እስራኤላውያንም እነዚህ ነበሩ፤
5. የእስራኤል የበኵር ልጅ የሆነው የሮቤል ዘሮች እነዚህ ነበሩ፤በሄኖኀ በኩል፣ የሄኖኀውያን ጐሣ፤በፈለስ በኩል፣ የፈሉሳውያን ጐሣ፤