ዘኁልቍ 25:16-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

17. “ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው።

18. ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለሠሩባችሁ ነው።”

ዘኁልቍ 25