13. ለአምላኩ (ኤሎሂም) ክብር ቀንቶ ለእስራኤላውያን ስላስተሰረየላቸው፣ እርሱና ልጆቹ ዘላቂ የክህነት ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል።
14. ከምድያማዊቷ ሴት ጋር የተገደለው እስራኤላዊ የሰሉ ልጅ ዘንበሪ ይባላል፤ የስምዖናውያን ቤተ ሰብ አለቃ ነበር።
15. እንዲሁም የተገደለችዋ ምድያማዊት ሴት ከስቢ ትባላለች፤ እርሷም ከምድያማውያን ቤተ ሰብ የአንዱ ነገድ አለቃ የሆነው የሱር ልጅ ነበረች።
16. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
17. “ምድያማውያንን እንደ ጠላት ቈጥራችሁ ፍጇቸው።
18. ይኸውም ፌጎር ላይ በተፈጸመው ድርጊትና በፌጎር ምክንያት በመጣው መቅሠፍት በተገደለችው በምድያማዊው አለቃ ልጅ፣ በእኅታቸው በከስቢ አታልለው የጠላትነት ሥራ ስለሠሩባችሁ ነው።”