ዘኁልቍ 23:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. በያዕቆብ ላይ የሚሠራ አስማት የለም፤በእስራኤልም ላይ የሚሠራ ሟርት አይኖርም፤ለያዕቆብና ለእስራኤል፣‘እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ያደረገውን እዩ!’ ይባልላቸዋል።

24. ሕዝቡ እንደ እንስት አንበሳ ይነሣል፤ያደነውን እስኪያነክት፣የገደለውንም ደም እስኪጠጣ፣እንደማያርፍ አንበሳ ሆኖ ይነሣል።”

25. በዚህ ጊዜ ባላቅ በለዓምን፣ “እንግዲያውስ ፈጽሞ አትርገማቸው፤ ፈጽሞም አትመርቃቸው!” አለው።

26. በለዓምም፣ “እግዚአብሔር (ያህዌ) የሚለኝን ሁሉ ማድረግ እንዳለብኝ አልነገርሁህምን?” ሲል መለሰለት።

27. ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን፣ “በል እንግዲያው ወደ ሌላ ቦታ ልውሰድህ፤ ከዚያ ሆነህ እንድትረግምልኝ ምናልባት እግዚአብሔር (ኤሎሂም) ይፈቅድልህ ይሆናል” አለው።

28. ባላቅም በለዓምን ምድረ በዳው ቍልቍል ወደሚታይበት ወደ ፌጎር ጫፍ አወጣው።

ዘኁልቍ 23