14. እንግዲህ በእግዚአብሔር (ያህዌ) የጦርነት መጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው በዚሁ የተነሣ ነው፤“ … በሱፋ ውስጥ የሚገኘው ዋሄብአርኖንና
15. ወደ ዔር የሚወስዱትበሞዓብ ድንበርም የሚገኙትየሸለቆች ተረተሮች።”
16. ከዚያም እግዚአብሔር (ያህዌ) ለሙሴ፣ “ሰዎቹን በአንድነት ሰብስባቸውና ውሃ እሰጣቸዋለሁ” ወዳለበት ብኤር ወደተባለው የውሃ ጒድጓድ ጒዞአቸውን ቀጠሉ።
17. ከዚያም እስራኤል ይህን መዝሙር ዘመረ፤“አንተ ምንጭ ሆይ ፍለቅ!እናንተም ዘምሩለት፤
18. ልዑላን ለቈፈሩት፣የሕዝብ አለቆች በበትረ መንግሥታቸውና በበትሮቻቸው ላጐደጐዱት፣የውሃ ጒድጓድ ዘምሩለት።”ከዚህ በኋላ ከምድረ በዳው ወደ መቴና ሄዱ፤
19. ከመቴና ወደ ነሃሊኤል፣ ከነሃሊኤልም ወደ ባሞት፣
20. ከባሞትም ፈስጋ ላይ ሆኖ ምድረ በዳው ቊልቊል ወደሚታይበት በሞዓብ ወደሚገኘው ሸለቆ ተጓዙ።
21. እስራኤል ወደ አሞራውያን ንጉሥ ወደ ሴዎን እንዲህ የሚሉ መልእክተኞች ላከ፤
22. “በአገርህ አልፈን እንድንሄድ ፍቀድልን፤ ወደ የትኛውም ዕርሻ ሆነ የወይን አትክልት አንገባም፤ ወይም ከየትኛውም ጒድጓድ ውሃ አንጠጣም። ከግዛትህ እስክንወጣ ድረስም የንጉሡን አውራ ጐዳና አንለቅም።”