ዘኁልቍ 20:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. የእግዚአብሔርን (ያህዌ) ማኅበረሰብ ወደዚህ ምድረ በዳ ያመጣችሁት ለምንድ ነው! ከነከብቶቻችን እዚሁ እንድናልቅ ነውን?

5. ከግብፅ አውጥታችሁ እህል ወይም በለስ፣ ወይን ወይም ሮማን ወደሌለበት ወደዚህ ክፉ ቦታ ያመጣችሁንስ ለምንድ ነው? የሚጠጣ ውሃ እንኳ ይታጣ!”

6. ሙሴና አሮን ከማኅበረ ሰቡ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሄደው በግንባራቸው ተደፉ፤ የእግዚአብሔርም (ያህዌ) ክብር ተገለጠላቸው።

7. እግዚአብሔርም (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤

ዘኁልቍ 20