ዘኁልቍ 2:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነው።

24. በየሰራዊታቸው ሆነው ከኤፍሬም ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ናቸው፤ እነዚህ ሦስተኛ ሆነው ይመጣሉ።

25. “በሰሜን በኩል የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣

26. የሰራዊቱም ብዛት ሥልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነው።

27. “የአሴር ነገድ ከእነዚህ ቀጥሎ ይሰፍራል፤ የአሴር ሕዝብ አለቃ የኤክራን ልጅ ፋግኤል ሲሆን፣

ዘኁልቍ 2