18. በምዕራብ በኩል የኤፍሬም ምድብ ሰራዊት በዐርማቸው ሥር ይሆናል፤ የኤፍሬም ሕዝብ አለቃ የዓሚሁድ ልጅ ኤሊሳማ ሲሆን፣
19. የሰራዊቱም ብዛት አርባ ሺህ አምስት መቶ ነው።
20. “ከእነዚህም የምናሴ ነገድ ይቀጥላል፣ የምናሴ ሕዝብ አለቃ የፍዳሱር ልጅ ገማልኤል ሲሆን፣
21. የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነው።
22. ከዚያም የብንያም ነገድ ይቀጥላል፣ የብንያም ሕዝብ አለቃ የጋዴዮን ልጅ አቢዳን ሲሆን፣
23. የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነው።
24. በየሰራዊታቸው ሆነው ከኤፍሬም ምድብ የተመዘገቡት ወንዶች በሙሉ አንድ መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ናቸው፤ እነዚህ ሦስተኛ ሆነው ይመጣሉ።
25. “በሰሜን በኩል የዳን ምድብ ሰራዊት በዐርማው ሥር ይሆናል፤ የዳን ሕዝብ አለቃ የአሚሳዳይ ልጅ አኪዔዘር ሲሆን፣
26. የሰራዊቱም ብዛት ሥልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነው።