ዘኁልቍ 2:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፤

2. “እስራኤላውያን ከምስክሩ ድንኳን ትይዩ ዙሪያውን ጥቂት ራቅ ብለው እያንዳንዱ ሰው በየዐርማውና በየቤተ ሰቡ ምልክት ሥር ይስፈር።”

3. “በምሥራቅ በኩል በፀሓይ መውጫ የይሁዳ ምድብ በየሰራዊቱና በዐርማቸው ሥር ይስፈር፤ የይሁዳ ሕዝብ አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን ነው፤

4. የሰራዊቱም ብዛት ሰባ አራት ሺህ ስድስት መቶ ነው።

ዘኁልቍ 2