ዘኁልቍ 12:8-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. እኔ ከእርሱ ጋር የምነጋገረው ፊት ለፊት ነው፤በግልጽ እንጂ በልዩ ዘይቤ አይደለም፤እርሱ የእግዚአብሔርን (ያህዌ) መልክ ያያል።ታዲያ እናንተ አገልጋዬን ሙሴንትቃወሙ ዘንድ ለምን አልፈራችሁም?”

9. የእግዚአብሔር (ያህዌ) ቍጣ በላያቸው ነደደ፤ እርሱም ትቶአቸው ሄደ።

10. ደመናው ከድንኳኑ ላይ በተነሣ ጊዜ፣ እነሆ፤ ማርያም በለምጽ ተመታች፤ እንደ በረዶም ነጣች። አሮንም ወደ እርሷ ዘወር ሲል ለምጽ ወርሶአት አየ፤

ዘኁልቍ 12