ዘኁልቍ 1:29-48 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. ከይሳኮር ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ አራት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

30. ከዛብሎን ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ አመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

31. ከዛብሎን ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ ሰባት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

32. ከዮሴፍ ልጆች፦ከኤፍሬም ዝርያ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

33. ከኤፍሬም ነገድ የተቈጠሩትም አርባ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

34. ከምናሴ ዝርያዎች፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

35. ከምናሴ ነገድ የተቈጠሩትም ሠላሳ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ነበሩ።

36. ከብንያም ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ፤

37. ከብንያም ነገድ የተቈጠሩትም ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

38. ከዳን ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

39. ከዳን ነገድ የተቈጠሩትም ሥልሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ።

40. ከአሴር ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

41. ከአሴር ነገድ የተቈጠሩት አርባ አንድ ሺህ አምስት መቶ ነበሩ።

42. ከንፍታሌም ዝርያ፦ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ በየጐሣቸውና፣ በየቤተ ሰባቸው መዝገብ መሠረት ስማቸው አንድ በአንድ ተጻፈ።

43. ከንፍታሌም ነገድ የተቈጠሩትም አምሳ ሦስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ።

44. በሙሴና በአሮን፣ እያንዳንዳቸውም ቤተ ሰባቸውን በወከሉት በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል አለቆች የተቈጠሩት ወንዶች እነዚህ ናቸው።

45. ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ዕድሜያቸው ሃያ ዓመትና ከዚያም በላይ ሆኖ በእስራኤል ሰራዊት ውስጥ ለመዋጋት ብቁ የሆኑት በየቤተ ሰባቸው ተቈጠሩ፤

46. ጠቅላላ ቍጥራቸውም ስድስት መቶ ሦስት ሺህ አምስት መቶ አምሳ ነበር።

47. የሌዊ ነገድ ቤተ ሰቦች ግን ከሌሎች ጋር አብረው አልተቈጠሩም፤

48. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ ብሎት ነበርና፤

ዘኁልቍ 1