ዘኁልቍ 1:2-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “የወንዶቹን ስም አንድ በአንድ በመዘርዘር መላውን የእስራኤል ማኅበረሰብ በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው ቍጠሯቸው።

3. በመላው እስራኤል ያሉትን ዕድሜያቸው ሃያና ከዚያም በላይ ሆኖ ለውጊያ ብቁ የሆኑትን ወንዶች ሁሉ አንተና አሮን በየምድባቸው ቍጠሯቸው።

4. ከየነገዱ የአባቶች ቤት ተጠሪ የሆነ አንድ ሰው ከእናንተ ጋር ይሁን።

5. የሚረዷችሁም ሰዎች ስም የሚከተለው ነው፦“ከሮቤል የሰዲዮር ልጅ ኤሊሱር፤

6. ከስምዖን የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤

7. ከይሁዳ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን፤

ዘኁልቍ 1