28. “ ‘ነገር ግን ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ተለይቶ የተሰጠ ማንኛውም ነገር፦ ሰውም ሆነ እንስሳ ወይም በውርስ የተገኘ መሬት አይሸጥም፤ አይዋጅምም። ለእግዚአብሔር (ያህዌ) የተሰጠ ማንኛውም ነገር እጅግ የተቀደሰ ነውና።
29. “ ‘እንዲጠፋ የተወሰነ ማንኛውም ሰው አይዋጅም፤ መገደል አለበት።
30. “ ‘ከዕርሻ ምርትም ሆነ ከዛፍ ፍሬ፣ ማንኛውም ከምድሪቱ የሚገኝ ዐሥራት የእግዚአብሔር (ያህዌ) ነው፤ ለእግዚአብሔርም (ያህዌ) የተቀደሰ ነው።