1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤
2. “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ተናገር፤ ‘ማንኛውም ሰው ተመጣጣኙን ዋጋ በመክፈል ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ሰውን ለመስጠት የተለየ ስእለት ቢሳል፣
3. ዕድሜው ከሃያ እስከ ሥልሳ ዓመት ለሆነ ወንድ፣ በቤተ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መሠረት፣ ግምቱ አምሳ ጥሬ ሰቅል ብር ይሁን።
4. ለሴት ከሆነ ግምቱ ሠላሳ ሰቅል ይሁን።
5. ዕድሜው ከአምስት እስከ ሃያ ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ ሃያ ሰቅል፣ ሴት ከሆነች ግምቷ ዐሥር ሰቅል ይሁን።
6. ዕድሜው ከአንድ ወር እስከ አምስት ዓመት ለሆነ ሰው፣ ወንድ ከሆነ ግምቱ አምስት ሰቅል ጥሬ ብር፣ ለሴት ከሆነ ሦስት ሰቅል ጥሬ ብር ይሁን።