ዘሌዋውያን 26:13-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ለግብፃውያን ባሪያዎች እንዳትሆኑ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ፤ የባርነት ቀንበራችሁን ሰብሬ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።

14. “ ‘ነገር ግን ባትሰሙኝ፣ እነዚህን ትዕዛዛት ባትጠብቁ፣

15. ሥርዐቴን ብትንቁ፣ ሕጌን ብታቃልሉ፣ ትእዛዛቴንም ሁሉ ባለመፈጸም ቃል ኪዳኔን ብታፈርሱ፣

16. እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኩሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።

ዘሌዋውያን 26