1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤
2. ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣
3. እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።
4. ከእርሱ ጋር በጋብቻ ለሚዛመዱት ግን ራሱን አያርክስ።
5. “ ‘ካህናት ዐናታቸውን አይላጩ፤ የጢማቸውን ዙሪያ አይላጩ፤ ሰውነታቸውንም አይንጩ፤