ዘሌዋውያን 21:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር (ያህዌ) ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ለካህናቱ ለአሮን ልጆች ንገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ማንኛውም ሰው ከዘመዶቹ መካከል ስለ ሞተው ሰው ራሱን አያርክስ፤

2. ነገር ግን የቅርብ ዘመዶቹ ስለሆኑት እናቱ፣ አባቱ፣ ወንድ ልጁ፣ ሴት ልጁ፣ ወይም ወንድሙ፣

3. እንዲሁም ባለማግባቷ ከእርሱ ጋር ስለ ምትኖር እኅቱ ራሱን ሊያረክስ ይችላል።

ዘሌዋውያን 21