4. “ ‘በማብሰያ ምድጃ የተጋገረ የእህል ቊርባን በምታቀርብበት ጊዜ፣ ከላመ ዱቄት ተዘጋጅቶ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ኅብስት ይሁን፤ አለዚያም ያለ እርሾ በስሱ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ቂጣ ይሁን።
5. የእህል ቊርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት ከተለወሰ ከላመ ዱቄት ይዘጋጅ።
6. ቈራርሰህ ዘይት አፍስበት፤ ይህ የእህል ቊርባን ነው።
7. የእህል ቊርባንህ በመጥበሻ የሚበስል ከሆነ፣ ከላመ ዱቄትና ከዘይት ይዘጋጅ።
8. በዚህ ሁኔታ የተዘጋጀውን የእህል ቊርባን ወደ እግዚአብሔር (ያህዌ) አምጥተህ ለካህኑ አስረክብ፤ ካህኑም ወደ መሠዊያው ይወስደዋል፤