ዘሌዋውያን 19:25-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. በአምስተኛው ዓመት ግን ፍሬውን ትበላላችሁ፤ በዚህም ሁኔታ ፍሬው ይበዛላችኋል፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ (ያህዌ ኤሎሂም) ነኝ።

26. “ ‘ደም ያለበትን ማንኛውንም ሥጋ አትብሉ፤“ ‘ጥንቈላ ወይም አስማት አትሥሩ።

27. “ ‘የራስ ጠጒራችሁን ዙሪያ አትከርከሙ፤ ጢማችሁንም አሳጥራችሁ አትቊረጡ።

ዘሌዋውያን 19