ዘሌዋውያን 17:7-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ከዚህ በፊት ላመነዘሩባቸው አጋንንት ከእንግዲህ ወዲህ ማንኛውንም መሥዋዕት ሊሠዉ አይገባም። ይህ ለእነርሱና ከእነርሱ በኋላ ለሚነሣው ትውልድ ሁሉ የዘላለም ሥርዐት ይሁን።’

8. “እንዲህም በላቸው፤ ‘የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም ሌላ መሥዋዕት የሚያቀርብ ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ፣

9. ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ለእግዚአብሔር (ያህዌ) ባያቀርብ፣ ያ ሰው ከወገኖቹ ተለይቶ ይጥፋ።

10. “ ‘ማንኛውም እስራኤላዊ ወይም በመካከላቸው የሚኖር ማንኛውም መጻተኛ ደም ቢበላ፣ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፤ ከወገኖቹም ለይቼ አጠፋዋለሁ፤

ዘሌዋውያን 17