ዘሌዋውያን 15:31-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. “ ‘በመካከላቸው ያለችውን ማደሪያዬን እንዳያረክሱና በርኵሰታቸው እንዳይሞቱ፣ እስራኤላውያንን ከሚያረክሳቸው ነገር ለዩአቸው።’ ”

32. ፈሳሽ ነገር የሚወጣውን፣ ዘሩም በመፍሰሱ ርኩስ የሆነውን ሰው ሁሉ፣

33. በወር አበባ ላይ ያለችን ሴት፣ ፈሳሽ ነገር የሚወጣቸውን ወንድ ወይም ሴት፣ በሥርዐቱ መሠረት ርኩስ ከሆነች ሴት ጋር የሚተኛውን ወንድ በሚመለከት ሕጉ ይኸው ነው።

ዘሌዋውያን 15