ዘሌዋውያን 13:35-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

35. ንጹሕ መሆኑ ከተገለጠ በኋላ ግን የሚያሳክከው ቊስል ተስፋፍቶ ቢገኝ፣

36. ካህኑ ይመርምረው፤ ቊስሉ በቈዳው ላይ ከሰፋ፣ ካህኑ የጠጒሩን ቢጫ መሆን አለመሆን ማየት አያሻውም፤ ሰውየው ርኩስ ነው።

37. ነገር ግን ቊስሉ በካህኑ አመለካከት ለውጥ ያላሳየ ከሆነና በውስጡ ጥቊር ጠጒር ካበቀለ ቊስሉ ድኖአል፤ ሰውየው ነጽቶአል፤ ካህኑም ንጹሕ መሆኑን ያስታውቅ።

38. “በወንድ ወይም በሴት ቈዳ ላይ ቋቍቻ ቢወጣ፣

39. ካህኑ ይመርምራቸው፤ ቋቍቻው ዳለቻ ከሆነ በቈዳ ላይ የወጣ ጒዳት የማያስከትል ችፍታ ነው፤ ሰውየውም ንጹሕ ነው።

ዘሌዋውያን 13