ዘሌዋውያን 11:13-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. “ ‘ከአዕዋፍ ወገን እነዚህን ትጸየፋላችሁ፤ ጸያፍ ስለ ሆኑም አትብሏቸው፦ ንስር፣ ጥንብ አንሣ፣ ግልገል አንሣ፣

14. ጭላት፣ ማንኛውም ዐይነት ጭልፊት፣

15. ማንኛውም ዐይነት ቊራ፣

16. ሰጐን፣ ጠላቋ፣ ዝይ፣ ማንኛውም ዐይነት በቋል፣

17. ጒጒት፣ ርኩም፣ ጋጋኖ፣

18. የውሃ ዶሮ፣ ይብራ፣ ስደተኛ አሞራ፣

19. ሽመላ፣ ማንኛውም ዐይነት ሳቢሳ፣ ጅንጁላቴ ወፍና የሌሊት ወፍ።

20. “ ‘ክንፍ ኖሮአቸው በአራት እግር የሚንቀሳቀሱ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ አስጸያፊዎች ይሁኑ።

ዘሌዋውያን 11