ዕዝራ 8:34-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ሁሉም ነገር ተቈጠረ፤ ተመዘነም፤ የተመዘነውም ሁሉ በዚያኑ ጊዜ ተመዘገበ።

35. ከዚያም ከምርኮ የተመለሱት፣ ለእስራኤል ሁሉ ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችን፣ ዘጠና ስድስት አውራ በጎችን፣ ሰባ ሰባት ተባዕት ጠቦቶችን፣ ለእስራኤል አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ ለኀጢአት መሥዋዕት ደግሞ ዐሥራ ሁለት ተባዕት ፍየሎችን አቀረቡ፤ ይህም ሁሉ ለእግዚአብሔር የቀረበ የሚቃጠል መሥዋዕት ነበር።

36. የንጉሡንም ትእዛዝ ለንጉሡ እንደራሴዎችና በኤፍራጥስ ማዶ ለሚገኙት አገረ ገዦች ሰጡ፤ እነርሱም ሕዝቡንና የእግዚአብሔርን ቤት ረዱ።

ዕዝራ 8