ዕንባቆም 3:17-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ምንም እንኳ የበለስ ዛፍ ባያፈራ፣ከወይን ተክልም ፍሬ ባይገኝ፣የወይራም ዛፍ ፍሬ ባይሰጥ፣ዕርሻዎችም ሰብል ባይሰጡ፣የበጎች ጒረኖ እንኳ ባዶውን ቢቀር፣ላሞችም በበረት ውስጥ ባይገኙ፣

18. እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤በድነቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።

19. ጌታ እግዚአብሔር ኀይሌ ነው፤እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።ለመዘምራን አለቃ፣ በባለ አውታር መሣሪያዎቼ የተዘመረ መዝሙር።

ዕንባቆም 3