ዕንባቆም 1:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሁሉም ለዐመፅ ታጥቀው ይመጣሉ።ሰራዊታቸው እንደ ምድረ በዳ ነፋስ ወደ ፊት ይገሠግሣል፤ምርኮኞችንም እንደ አሸዋ ይሰበስባል።

10. ነገሥታትን ይንቃል፤በገዦችም ላይ ያፌዛል፤በምሽግ ሁሉ ላይ ይሥቃል፤የዐፈር ቊልል ሠርቶም ይይዘዋል።

11. ከዚያም በኋላ እንደ ነፋስ ዐልፎ ይሄዳል፤ጒልበታቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ ከዘላለም ጀምሮ ያለህ አይደለህምን?የእኔ አምላክ፣ የእኔ ቅዱስ እኛ አንሞትም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንዲፈርዱ ሾመሃቸዋል፤ዐለት ሆይ፤ ይቀጡ ዘንድ ሥልጣን ሰጠሃቸው።

ዕንባቆም 1