ዕብራውያን 7:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. እንዲህ ተብሎ ተመስክሮለታል፤“እንደ መልከጼዴቅ ሹመት፣አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።”

18. የቀድሞው ትእዛዝ ደካማና የማይጠቅም በመሆኑ ተሽሮአል፤

19. ሕጉ ማንንም ፍጹም ሊያደርግ ስለማይችል ወደ እግዚአብሔር የምንቀርብበት የተሻለ ተስፋ መጥቶአል።

20. ይህ ያለ መሐላ አልሆነም፤ ሌሎች ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤

21. እርሱ ግን ካህን የሆነው በመሐላ ነው፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮለታል፤“ጌታ ማለ፤ዐሳቡንም አይለውጥም፤‘አንተ ለዘላለም ካህን ነህ።’ ”

22. ከዚህ መሐላ የተነሣ፣ ኢየሱስ ለተሻለ ኪዳን ዋስ ሆኖአል።

ዕብራውያን 7