ዕብራውያን 3:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. በምድረ በዳ በፈተና ቀን፣በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣ልባችሁን አታደንድኑ።

9. አባቶቻችሁ በዚያ ተፈታተኑኝ፤መረመሩኝ፤ ያደረግሁትንም ሁሉ ለአርባ ዓመት አዩ።

10. በዚያም ትውልድ ላይ የተቈጣሁት ለዚህ ነበር፤እንዲህም አልሁ፤ ‘ልባቸው ሁል ጊዜ ይስታል፤መንገዴንም አላወቁም፤’

11. ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”

12. ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

13. ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

14. በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ተካፋዮች እንሆናለን፤

ዕብራውያን 3