ዕብራውያን 3:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ስለዚህ በቍጣዬ እንዲህ ብዬ ማልሁ፤“ወደ ዕረፍቴ ከቶ አይገቡም።”

12. ወንድሞች ሆይ፤ ከእናንተ ማንም ከሕያው እግዚአብሔር የሚያስኰበልል፣ ኀጢአተኛና የማያምን ልብ እንዳይኖረው ተጠንቀቁ።

13. ነገር ግን ከመካከላችሁ ማንም በኀጢአት ተታሎ ልቡ እንዳይደነድን፣ “ዛሬ” እየተባለ ሳለ በየቀኑ እርስ በርሳችሁ ተጽናኑ።

14. በመጀመሪያ የነበረንን እምነት እስከ መጨረሻው አጽንተን ብንይዝ ከክርስቶስ ጋር ተካፋዮች እንሆናለን፤

15. ይኸውም፣“ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ፣በዐመፅ እንዳደረጋችሁት፣አሁንም ልባችሁን አታደንድኑ” እንደ ተባለው ነው።

16. ሰምተው ያመፁት እነማን ነበሩ? ሙሴ ከግብፅ መርቶ ያወጣቸው ሁሉ አይደሉምን?

ዕብራውያን 3