ዕብራውያን 10:37-39 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. ምክንያቱም ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣“የሚመጣው እርሱ ይመጣል፤ አይዘገይም።

38. ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል፤ወደ ኋላ ቢያፈገፍግ፣ነፍሴ በእርሱ ደስ አትሰኝም።”

39. እኛ ግን አምነው ከሚድኑት ወገን እንጂ፣ ወደ ኋላ አፈግፍገው ከሚጠፉት አይደለንም።

ዕብራውያን 10