ዕብራውያን 1:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ስለ መላእክትም ሲናገር፣“መላእክቱን ነፋሳት፣አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።

8. ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤

9. ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣የደስታንም ዘይት ቀባህ።”

ዕብራውያን 1