7. ስለ መላእክትም ሲናገር፣“መላእክቱን ነፋሳት፣አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል ያደርጋል” ይላል።
8. ስለ ልጁ ግን እንዲህ ይላል፤“አምላክ ሆይ፤ ዙፋንህ ከዘላለም እስከ ዘላለም ጸንቶ ይኖራል፤ጽድቅም የመንግሥትህ በትር ይሆናል፤
9. ጽድቅን ወደድህ፤ ዐመፃን ጠላህ፤ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ከባልንጀሮችህ በላይ አስቀመጠህ፣የደስታንም ዘይት ቀባህ።”
10. ደግሞም እንዲህ ይላል፤ “ጌታ ሆይ፤ አንተበመጀመሪያ የምድርን መሠረት አኖርህ፤ሰማያትም የእጆችህ ሥራ ናቸው።
11. እነርሱ ይጠፋሉ፤ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፤
12. እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”
13. እግዚአብሔር፣“ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?