ዕብራውያን 1:12-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. እንደ መጐናጸፊያ ትጠቀልላቸዋለህ፤እንደ ልብስም ይለወጣሉ።አንተ ግን ያው አንተ ነህ፤ዘመንህም ፍጻሜ የለውም።”

13. እግዚአብሔር፣“ጠላቶችህን የእግርህ መርገጫ እስከማደርግልህ ድረስ፣በቀኜ ተቀመጥ” ያለው ከመላእክት ከቶ ለማን ነው?

14. መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን?

ዕብራውያን 1