17. “እነሆ፤ በመካከላችሁ መርዘኛ እባቦችን፣የአስማተኛ ብልኀት የማይገታቸው እፉኝቶችን እሰዳለሁ፤እነርሱም ይነድፉአችኋል፤”ይላል እግዚአብሔር።
18. በሐዘኔ የምታጽናናኝ ሆይ፤ልቤ በውስጤ ዝላለች።
19. እንዲህ የሚለውን የሕዝቤን ጩኸት፣ከሩቅ ምድር ስማ፦ እግዚአብሔር በጽዮን የለምን?ንጉሥዋስ በዚያ አይኖርምን?”“በተቀረጹ ምስሎቻቸው፣እንዲሁም ከንቱ በሆኑ ባዕዳን ለምን አስቈጡኝ?”
20. “መከሩ ዐለፈ፤በጋው አበቃ፤እኛም አልዳንም።”
21. ሕዝቤ ሲቈስል፣እኔም ቈሰልሁ፤አለቀስሁ፤ ድንጋጤ ያዘኝ።
22. በገለዓድ የሚቀባ መድኀኒት የለምን?ወይስ በዚያ ሐኪም አልነበረምን?ለሕዝቤ ቍስል፣ለምን ፈውስ አልተገኘም?