ኤርምያስ 52:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሴዴቅያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ አንድ ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ የእናቱም ስም አሚጣል ሲሆን፣ እርሷም የሊብና ሰው የኤርምያስ ልጅ ነበረች።

2. ሴዴቅያስም ኢዮአቄም እንዳደረገው ሁሉ፣ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

3. እግዚአብሔር በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ላይ ይህን ሁሉ ያደረሰውንና በመጨረሻም ከፊቱ ያስወገዳቸው ከቍጣው የተነሣ ነበር።ሴዴቅያስም በባቢሎን ንጉሥ ላይ ዐመፀ።

ኤርምያስ 52