ኤርምያስ 51:41-43 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

41. “ሼሻክ እንዴት ተማረከች!የምድር ሁሉ ትምክህትስ እንዴት ተያዘች!ባቢሎን በሕዝብ ሁሉ ዘንድ፣ምንኛ አስደንጋጭ ሆነች።

42. ባሕር በባቢሎን ላይ ይወጣል፤ሞገዱም እየተመመ ይሸፍናታል።

43. ከተሞቿ ሰው የማይኖርባቸው፣ዝርም የማይልባቸው፣ደረቅና በረሓማ ቦታ፣ባድማ ምድርም ይሆናሉ።

ኤርምያስ 51