ኤርምያስ 50:5-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ወደ ጽዮን የሚወስደውን መንገድ ይጠይቃሉ፤ፊታቸውንም ወደዚያ ያቀናሉ።መጥተውም ከቶ በማይረሳ፣በዘላለም ቃል ኪዳን፣ ከእግዚአብሔር ጋር ይጣበቃሉ።

6. “ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤እረኞቻቸው አሳቷቸው፤በተራሮችም ላይ እንዲቅበዘበዙ አደረጓቸው፤በተራራና በኰረብታ ላይ ተንከራተቱ፤ማደሪያቸውንም ረሱ።

7. ያገኛቸው ሁሉ ይውጣቸዋል፤ጠላቶቻቸውም፣ ‘እኛ በደለኞች አይደለንም፤እነርሱ የአባቶቻቸውን ተስፋ እግዚአብሔርን፣እውነተኛ ማደሪያቸው የሆነውን እግዚአብሔርን በድለዋል’ አሉ።

8. “ከባቢሎን ሽሹ፤የባቢሎናውያንን ምድር ልቀቁ፤መንጋ እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ።

ኤርምያስ 50