“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ?ልጆችሽ ትተውኛል፤እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።