ኤርምያስ 48:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ክፉኛ እያለቀሱ፣ወደ ሉሒት ሽቅብ ይወጣሉ፤ስለ ደረሰባቸውም ጥፋት መራራ ጩኸት እያሰሙ፣ወደ ሖርናይም ቍልቍል ይወርዳሉ።

6. ሽሹ፤ ሕይወታችሁንም አትርፉ!በምድረ በዳ እንዳለ ቍጥቋጦ ሁኑ።

7. በድርጊታችሁና በብልጽግናችሁ ስለምትታመኑ፣እናንተም ትማረካላችሁ፣ካሞሽም ከካህናቱና ከመኳንንቱ ጋር፣በምርኮ ይወሰዳል።

8. በእያንዳንዱ ከተማ ላይ አጥፊ ይመጣል፤አንድም ከተማ አያመልጥም። እግዚአብሔር ተናግሮአልና፣ሸለቆው ይጠፋል፤ዐምባውም ይፈርሳል።

9. በራ እንድታመልጥ፣ለሞዓብ ክንፍ ስጧት፤ከተሞቿም ምንም እስከማይኖርባቸው ድረስ፣ባድማ ይሆናሉ።

ኤርምያስ 48