ኤርምያስ 48:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35. በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

36. “ስለዚህ ልቤ ለሞዓብ እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም እንደ ዋሽንት ያንጐራጒራል።ያከማቹት ንብረት ጠፍቶአልና።

37. የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

ኤርምያስ 48