ኤርምያስ 48:31-35 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

31. ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ።

32. የሴባማ ወይን ሆይ፤ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣አጥፊው መጥቶአል።

33. ከሞዓብ የአትክልት ቦታና እርሻ፣ሐሤትና ደስታ ርቆአል፤የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣የእልልታ ድምፅ አይደለም።

34. “ከሐሴቦን እስከ ኤልያሊና እስከ ያሀጽ፣ከዞዓር እስከ ሖሮናይም፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ድረስ፣ጩኸታቸው ከፍ ብሎ ይሰማል፤የኔሞሬም ውሃ እንኳ ደርቆአልና።

35. በመስገጃ ኰረብቶች ላይ የሚሠዉትን፣ለአማልክታቸው የሚያጥኑትን፣ከሞዓብ አጠፋለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር፤

ኤርምያስ 48