ኤርምያስ 48:27-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. በእስራኤል ላይ ስታላግጥ አልነበረምን?ስለ እርሷ በተናገርህ ቍጥር፣እያቃለልሃት ራስህን የምትነቀንቀውስ፣ከሌቦች ጋር ስትሰርቅ ተይዛለችን?

28. እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣እንደ ርግብ ሁኑ።

29. “ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

30. መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤”ይላል እግዚአብሔር።“ጒራውም ፋይዳ አይኖረውም።

ኤርምያስ 48