20. ሞዓብ በመፍረሱ ተዋርዷል፤ዋይ በሉ፤ ጩኹ፤የሞዓብን መደምሰስ፣በአርኖን አጠገብ አስታውቁ።
21. ፍርድ በዐምባው ምድር፦በሖሎን፣ በያሳና በሜፍዓት ላይ፣
22. በዲቦን፣ በናባውና በቤት ዲብላታይም ላይ፣
23. በቂርያታይም፣ በቤት ጋሙልና በቤትምዖን ላይ፣
24. በቂርዮትና በባሶራ ላይ፤በሩቅና በቅርብ፣ ባሉት በሞዓብ ከተሞች ሁሉ ላይ መጥቶአል።
25. የሞዓብ ቀንድ ተቈርጦአል፤እጁም ተሰባብሮአል፤”ይላል እግዚአብሔር።