ኤርምያስ 46:27-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. “አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤እስራኤል ሆይ፤ አትሸበር፤አንተን ከሩቅ ስፍራ፣ዘርህንም ተማርኮ ከሄደበት ምድር አድናለሁ።ያዕቆብም ተመልሶ በሰላምና በርጋታ ይቀመጣል፤የሚያስፈራውም አይኖርም።

28. አገልጋዬ ያዕቆብ ሆይ፤ አትፍራ፤እኔ ከአንተ ጋር ነኝና” ይላል እግዚአብሔር፤“አንተን የበተንሁበትን ሕዝብ ሁሉ፣ፈጽሜ ባጠፋም እንኳ፣አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም።ተገቢውን ቅጣት እሰጥሃለሁ እንጂ፣ያለ ቅጣት አልተውህም።

ኤርምያስ 46