ኤርምያስ 46:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. “ግብፅ ያማረች ጊደር ናት፣ነገር ግን ተናዳፊ ዝንብ፣ከሰሜን ይመጣባታል።

21. ቅጥረኞች ወታደሮቿም፣እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤የሚቀጡበት ጊዜ ስለ ደረሰ፣ጥፋታቸው ስለ ተቃረበ፣እነርሱም ወደ ኋላ ተመልሰው በአንድነት ይሸሻሉ፣በቦታቸውም ጸንተው ሊቋቋሙ አይችሉም።

22. ጠላት ገፍቶ ሲመጣባት፣ግብፅ እንደሚሸሽ እባብ ታፏጫለች፤ዛፍ እንደሚቈርጡ ሰዎች፣መጥረቢያ ይዘው ይመጡባታል።

23. ጥቅጥቅ ጫካ ቢሆንም፣ ደን ይመነጥራሉ፤”ይላል እግዚአብሔር፤“ብዛታቸው እንደ አንበጣ ነው፤ሊቈጠሩም አይችሉም።

ኤርምያስ 46