ኤርምያስ 46:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ስለ ሕዝቦች ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤

2. ስለ ግብፅ፤ በይሁዳ ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመነ መንግሥት በአራተኛው ዓመት በኤፍራጥስ ወንዝ በከርከሚሽ የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ባሸነፈው በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ኒካዑ ሰራዊት ላይ የተነገረ መልእክት ይህ ነው፤

3. “ትልቁንና ትንሹን ጋሻ አዘጋጁ፤ለውጊያም ውጡ

4. ፈረሶችን ጫኑ፤በላያቸውም ተቀመጡ፤የራስ ቍር ደፍታችሁ፣በየቦታችሁ ቁሙ፤ጦራችሁን ወልውሉ፤ጥሩራችሁን ልበሱ

5. ነገር ግን ይህ የማየው ምንድ ነው?እጅግ ፈርተዋል፤ወደ ኋላ እያፈገፈጉ ነው፤ብርቱ ጦረኞቻቸው ተሸንፈዋል፤ዘወር ብለውም ሳያዩ፣በፍጥነት እየሸሹ ነው፤በየቦታውም ሽብር አለ፣”ይላል እግዚአብሔር።

6. “ፈጣኑ መሸሽ አይችልም፤ብርቱውም አያመልጥም፤በሰሜን በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ፣ተሰናክለው ወደቁ።

7. “ይህ እንደ ዐባይ ወንዝ ሙላት የሚዘለው፣እንደ ደራሽ ወንዝ የሚፈሰው ማነው?

ኤርምያስ 46